በቦስተንና አትላንታ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ113 ህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ


ሐምሌ 26/2013 (ዋልታ)
– በቦስተንና አትላንታ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በተደረጉ የበይነ መረብ ውይይቶች ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ113 ሽህ ዶላር በላይ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የድርድር ሂደትና ዳያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች እንዲሁም የኤምባሲ አገልግሎትና የኢንቨስትመንት ድጋፍም ተዳስሰዋል።

ከአትላንታ መድረክ ከ33 ሽህ ዶላር በላይ እንዲሁም ከቦስተን መድረክ 80 ሽህ ዶላር በአጠቃላይ ከ113 ሽህ ዶላር በላይ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በልገሳ መሰብሰቡን ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲየተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡