በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እና አሸባሪውን የህወሓት ቡድን የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 18/2013 (ዋልታ) – በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እና አሸባሪውን የህወሓት ቡድን የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

በጅማ፣ ባሌሮቤ፣ ሻሸመኔና በሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ህዝቡ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን ድጋፍና አሸባሪውን የህወሓት ቡድን የሚያወግዙ መፈክሮችን ይዞ ነው ሰልፍ መውጣቱን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡