በታላቁ ሩጫ ውድድር በወንዶች ገመቹ ዲዳ፤ በሴቶች ያለምዘርፍ የኋላው አሸነፉ

ጥር 16/2014 (ዋልታ) በዘንድሮው ታላቁ ሩጫ ውድድር በወንዶች አትሌት ገመቹ ዲዳ፤ በሴቶች አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸነፉ።
በ2014 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተደረገው ውድድር በወንዶች አትሌት ገመቹ ዲዳ 1ኛ፣ አትሌት ጌታነህ ሞላ 2ኛ እንዲሁም አትሌት ቦኪ ድሪባ 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በሴቶች ደግሞ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 1ኛ፣ አትሌት ግርማዊት ገብረእግዚአብሔር 2ኛ እንዲሁም አትሌት መልክናት ውዱ 3ኛ ደረጃን ይዘው ነው ያጠናቀቁት።
ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በርካታ ሕዝብ የሚሳተፍበት የስፖርት ፌስቲቫል ነው።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ሲሆን ከኢትዮጵያዊያን ባሻገር ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚመጡ የውጪ አገራት ዜጎች የሚሳተፉበት መሆኑ ይታወቃል።