በትግራይ  ክልል  የሚኖሩ  የሀይማኖት  አባቶች በሀገሪቱ  ሰላም  እንዲመጣ  ሃይማኖታዊ  ተልዕኳቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

የሀይማኖት  አባቶች

ነሐሴ 25/2013 (ዋልታ) – በትግራይ  ክልል  የሚኖሩ  የሀይማኖት  አባቶች በሀገሪቱ  ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ  ሃይማኖታዊ ተልዕኳቸውን መወጣት እንዳለባቸው የደባርቅ ከተማ ሀይማኖት አባቶች ጥሪ  አቀረቡ።

የግለሰቦችን ስልጣን ለማራዘም ትግራይ በሚገኝ መገናኛ ብዙሃን እየቀረቡ ከሁሉም ሀይማኖታዊ አስተምሮ የተቃረነ ጦርነት ቀስቃሽ ፕሮፓጋንዳ የሚያቀርቡ የሃይማኖት አባቶች  ከድርጊታቸው በመታቀብ ሃይማኖታዊ ተልዕኳተውን መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉም አሳስበዋል።

የሃይማኖት መሪዎች ቅዱሳት መጽሐፍት የሚያዙትን ሠላም፣ ፍቅር እና አንድነትን  ለተከታዮቻቸው በማስተማር ሃገሪቱ ካለችበት ሁኔታ እንድትወጣ የማድረግ ሚና እንዳለባቸውም የሃይማኖት  አባቶች ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ጥፋቶች ሳይደርሱ ይህ እንዲሆን አሁንም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የእምነት መሪዎች ያላቸውን ዕድል መጠቀምና ሀገር ወደ ሰላምና  አንድነት  እንድትመጣ  ሚናቸውን  መወጣት  እንዳለባቸው አመልክተዋል።

(በታሪኳ መንግስተአብ)