በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ በመሳተፍ ዲፕሎማ አገኘች

ሐምሌ 20/2013(ዋልታ) – በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ በመሳተፍ በ58 ኪ.ግ ምድብ 7ኛ በመያዝ ዲፕሎማ አግኝታለች፡፡

ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ የወከለው አትሌት ሰለሞን ቱፋ እየተካሄደ ባለው የቶኪዮ ኦሎምፒክ በ58 ኪ.ግ ምድብ ባደረገው ውድድር 7ኛ ደረጃ በመያዝ ዲፕሎማ መገኘቱን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡