በቻግኒ መጠለያ ካምፕ የነበሩ ተፈናቃዮች ወደ ተዘጋጀላቸው መጠለያ መንቀሳቀስ ጀመሩ

ሰኔ 11/2013 (ዋልታ) – ከመተከል ዞን ተፈናቅለው በቻግኒ መጠለያ ካምፕ የነበሩ የማንቡክ እና የማንዱራ ወረዳ ነዋሪዎች ወደ ተዘጋጀላቸው የየወረዳቸው መጠለያ መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡

የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ምክትል ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ተመላሾቹ ወደ ቀያቸው ሲመለሱ ኮማንድ ፖስቱ የሚጠበቅበትን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተፈናቀሉ ዜጎችን መመለስ የማይፈልጉ አንዳንድ አካላት መኖራቸውን የጠቆሙት ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ፥ “ለእነዚህ አካላት አሉባልታና የሃሰት ወሬ ሳትበገሩ ወደ ተዘጋጀላችሁ ስፍራ ለመሄድ ያሳያችሁት ተነሳሽነት የሚደነቅ ነው” ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።