በአራዳ ክፍለ ከተማ “ከመሪዬ ጋር እዘምታለሁ” በማለት ለወሰኑ ወጣቶች ሽኝት እየተካሄደ ነው

ኅዳር 16/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ “ከመሪዬ ጋር እዘምታለሁ” በማለት ለወሰኑ ወጣቶች ሽኝት እየተደረገላቸው ነው።

በመድረኩ ክፍለ ከተማው ለአገር መከላከያ ሰራዊት ያሰባሰበውን ገንዘብ እንደሚያስረክብም ተገልጿል፡፡

በዝግጁቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የጦር አዛዦች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ነዋሪዎች መገኘታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።