በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው

የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየተሰጠ ይገኛል።

በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም ችግር እየወሰዱ ሲሆን ፈተናው ለ3 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

የፈተና ደኅንነት ለመጠበቅ እና የፈተናውን ሂደት ለመከታተልም ቀደም ሲል የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት 10 የፀጥታ አካላት ማሰማራቱ ተጠቁሟል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በዚህም 71 ሺሕ 832 የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW