በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ሊትር ዘይት ለተጠቃሚው ይቀርባል

የካቲት 28/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ ከነገ ጀምሮ 6 ነጥብ 6 ሚሊየን ሊትር ዘይት ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርብ የከተማው ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

በተጨማሪም በመዲናዋ የኑሮ ወድነት እንዲባባስ ምክንያት የሆኑ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ቢሮው በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

የኑሮ ውድነትእንዲባባስ ከህገወጥ ነጋዴዎች ጋር በጋራ የሚሰሩ አመራሮች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑንም ተጠቅሷል፡፡

በዙፋን አምባቸው