በኢሬቻ ግርግር ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት የበዓሉን አስቤ ያልተረዱ ናቸው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መስከረም 21/2014 (ዋልታ) – የኢሬቻን በዓል ጠብቀው ግርግር ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት የኢሬቻን በዓል እስቤ ያልተረዱ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

‹‹ኢሬቻ ከጨለማ ወደ ብርሀን ስለመድረሳችን ለፈጣሪ ምስጋና የምንሰጥበት በዓል ነው›› ያሉት ከንቲባዋ የኢሬቻን በዓል ጠብቀው ግርግር ለመፍጠር የሚያስቡ አካላት ሰላም እንዳይሰፍን የሚፈልጉ ናቸው ብለዋል።

አክለውም የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ከበርካታ ፈተናዎች አልፈን በአዲስ ምዕረፍ ጉዞ የጀመርንበት በመሆኑ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

የኢሬቻን በዓል ስናከብር ህይወታቸውን ሰጥተው እኛ በነፃነት እንድንቀሳቀስ ላደረጉን ለአገር መከላከያ አባላት እንዲሁም ለፀጥታ ኃይሎች ክብር በመስጠት ሊሆን ይገባልም ብለዋል።

“ኢሬቻ የሰላም ተምሳሌት ነው” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል አስመልክቶ ሦስተኛው የሰላም ጉባኤ በአዲስ አበባ እየታካሄደ ነው።

በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አቢዲሳ፣ የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) እንዲሁም  ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።