በኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ የደረሰውን ጉዳት በሚመለከት ማብራሪያ እየተሰጠ ነው

የፍትህ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ጦርነት እና በሌሎችም የሀገሪቷ ክፍሎች የተፈጠሩ ግጭቶችን ተከትሎ በሰው እና ንብረት ላይ የደረሱ ጉዳቶችን በሚመለከት ለተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ማብራሪያ እየተሰጠ ነው።

መንግስት በተለይም የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ በአክሱም እና ማይካድራ ላይ ተፈፀሙ የተባሉ ሰብዓዊ ጉዳቶች እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ የደረሱ ጉዳቶችን የሚመለከቱ ምርመራዎችን እያደረገ ስለመሆኑ በማብራርያው ላይ ቀርቧል።

ከዚህም በተጨማሪ በሰው እና በንብረት ላይ የደረሱ ጉዳቶችን በመለየት እየተወሰዱ ስላሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ስራም በማብራሪያው ላይ ተካቷል።

እስካሁን እየተደረጉ ባሉ ምርመራዎች የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች የተሰበሰቡ ሲሆን ምርመራውም እንደቀጠለ ስለመሆኑ ተመላክቷል።

በሚልኪያስ አዱኛ