በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

ኅዳር 4/2014 (ዋልታ) – በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ17 ሺሕ ዮሮ በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ድጋፉ አሸባሪው ሕወሓት ወደ አጎራባች ክልሎች በመግባት ባደረሰው ወረራና ጥቃት የተጎዱ እና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት የሚውል ይሆናል።

ድጋፉን የተረከበው በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማሰባሰብ ሥራው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጥሪ አቅርቧል፡፡