በኦሮሚያ ክልል ትምህርት ተጀመረ

ጥቅምት 03/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ከዛሬ ጀምሮ 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩ ተገለጸ፡፡

እንደ ኦሮሚያ ክልል በ2014 ትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርኃግብር በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ከራ ሆራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሂዷል።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) ትምህርት መጀመሩን ባበሰሩበት ንግግር በዘንድሮ የትምህርት ዘመን በክልሉ 9.8 ሚሊዮን ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ይጀምራሉ ብለዋል።

እንደ ክልል በዘንድሮ የትምህርት ዘመን ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ የትምህርት አሰጣጡ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በክልሉ ከፀጥታ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ያልተመዘገቡ ተማሪዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ በመሆን እንዲመዘገቡ አስፈላጊው ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት።

በደረሰ አማረ