በኦሮሚያ ክልል የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርኃግብር እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 06/2013 (ዋልታ) – በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀምበር 351 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ በተለያዩ አካባቢዎች ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እየተከለ ይገኛል፡፡

በክልሉ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር አራት ነጥብ አንድ ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዟል።

በዛሬው እለት እስከጠዋቱ ሶስት ሰአት ድረስ ከሰባ ሚሊየን በላይ ችግኝ መተከሉን የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳልካቾ ተፈራ ገልጸዋል።

በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የኦሮሚያ ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶ/ር ግርማ አመንቴ የተመራው ልዑክ ቡድን በሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ ችግኝ ችግኝ መትከሉም ተገልጿል፡፡

በዞኑ በአንድ ጀንበር ከ15 ሚሊዮን ችግኞች በላይ ለመትከል ታቅዶ የዘመቻ ስራው ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ኦቢኤን ዘግቧል፡፡