በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሕዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

ጥር 16/2014 (ዋልታ) በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሕዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።

ኮንፈረንሱ ከብሔረሰብ አስተዳደሩ አጎራባች ሕዝብ ጋር ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር፣ በጦርነቱ የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ለማሳወቅ፣ በህልውና ዘመቻው ጀብድ የፈጸሙ አካላትን እውቅና ለመስጠትና ሕዝቡ ልማቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ ነው።

በኮንፈረንሱ የጦርነቱን ጉዳት የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቪሽንና ሌሎች ዝግጅቶች ለእይታ መቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በኮንፈረንሱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የብሔረሰብ አስተዳደሩ አጎራባች ዞንና ወረዳ የሥራ ኃላፊዎች፣ የአፋር ክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።