በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰላም ትምህርት እንዲሰጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

ነሀሴ 11/2013 (ዋልታ) – በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰላም ትምህርት እንዲሰጥ የሚያስችል ስምምነት የኢትዮጵያ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ከተባበሩት መንግስታት የሳይን የባህል ማዕከል (UNISCO) ጋር የጋራ ስምምነት ተፈርሟል።

ወጣቱ የሰላም አስፈላጊነት እንዲረዳ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሰላም ትምህርት  በትምህርት መልክ መሰጠቱ ጉልህ ሚና እንዳለው በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

ስምምነቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች በተገኙበት ከጃፖን መንግስት እንዲሁም ከዮኔስኮ ጋር በጋራ በመሆን ተፈርሞል፡፡

የግጭት ቀጠና ናቸው ተብለው በተመረጡ 6 ዩኒቨርስቲዎች ትምህርቱን እንደመጀመርያ ለመስጠት መታሰቡም ተነግሯል።

የሰላም ትምህርቱ ለተማሪዎች በሚማሩበት ማህበረሰብ የግጭት አፈታት መንገድ ተምረው እንዲሁም የሰላም ፋይዳውን የሚያትት እንደሚሆን ተገልጿል።

(በዙፋን አምባቸው)