በክልሉ ለከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች የዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊነት ሹመት ተሰጠ

የካቲት 8/2014 (ዋልታ) በአማራ ክልል የተሻለ የሥራ አፈጻጸም፣ የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ላላቸው ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች የዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊነት ሹመት ተሰጣቸው።

በዚህም ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አትንኩት አያሌው ጌታሁን፣ ለደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እርገጤ ጌታሁን ተስፋዬ እንዲሁም ለሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ወረታው ዓለም አግደው ተመድበዋል፡፡

በተጨማሪም ኮማንደር ክንዴ ዓለማየሁ ደስታ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ እና ኮማንደር አሳምነው ሙላት ደፋሩ የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ሆነው መመደባቸውን ከአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡