በኮንታ የኅልውና ዘመቻውን የሚደግፍ እና የአሸባሪው ሕወሓት የሚቃወም ሰልፍ ተካሄደ

ኅዳር 4/2014 (ዋልታ) በኮንታ ልዩ ወረዳ አመያና ጭዳ ከተማ አስተዳደር የኅልውና ዘመቻውን የሚደግፍ እና የአሸባሪውን ሕወሓት ቡድን የሚቃወም ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ፡፡
በሕዝባዊ ሰልፉ የአሸባሪው የሕዋሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ኢሰብኣዊ ጭፍጨፋ በማስታወስ የህሊና ፀሎት በማድረግ ለአገር አንድነት ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በአንድነት እንዲቆም ተጠይቋል።
ነዋሪዎቹ “አገራችን ክብራችን፣ የምንኖርባት መጠለያችን ናት!፣ በእርሷ የመጣብንን አንላቀቅም ህይወታችንን መስዕዋት እስከ መክፈል እንታገላለን፣ ስለ ኢትዮጵያ የሚንበረከክ ጉልበት የለንም፣ ሽንፈት ታሪካችን አይደለም” የሚሉ መፈክሮችን አስተጋብተዋል።
በሰልፉ የተገኙት የኮንታ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ፋንታሁን ብላቴ አሸባሪው ሕወሓት አገሩን ለማፍረስ ቢነሳም ተግባሩ አይሳካለትም፤ እኛ ኢትዮጵያዊያን የኮንታ ሕዝብ በአንዲቷ ኢትዮጵያ ከመጡብን ግን የምንሰስተው ነገር የለንም፤ ይህንን ፈተና አልፈን የኢትዮጵያን ትንሳኤ በአጭር ጊዜ እናረጋግጣለን ብለዋል።
በሰልፉ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ የአገር የሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
መረጃው የኮንታ ልዩ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ነው።