በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች አቀባበል እየተደረገ ነው

ግንቦት 9/2014 (ዋልታ) የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለ10ኛ ጊዜ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ለተመደቡ ከ4 ሺሕ 500 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አቀባበል እያደረገ ነው፡፡

በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የዋቸሞ  ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ሌሎች  የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አደረጃጀት እንዲሁም የከተማው ማኅበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ዩኒቨርሲቲው በቅርብ ጊዜ ተመስርቶ የመማር ማስተማሩን ሥራ የጀመረ ዩኒቨርሲቲ ቢሆንም በርካታ ሀገር ዐቀፍና ክልላዊ ድሎችን የተጎናፀፈ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሰላም ወዳድ ማኅበረሰብ የሚገኝበትና የሰላም አምባሳደር የሆነ ግቢ እንደሆነ መናገራቸውን ከዩኚቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡