በየም ልዩ ወረዳ ለመከላከያ ሰራዊቱ እና ጥምር ሀይሉ የስንቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) በደቡብ ክልል የየም ልዩ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ሀገርን ከጠላት ወረራ ለመጠበቅ እየተፋለሙ ላሉት ጀግኖች የስንቅ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡

በልዩ ወረዳው ሳጃ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚሆን የስንቅ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡

በስንቅ ዝግጅቱ የተሳተፉት የልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ሳሙኤል ገበረሚካኤል እንደገለጹት፤ ሀገርን ለማዳን የሚደረገው ርብርብ ለመደገፍ ከፊት በመሰለፍ የሚጠበቅብንን ለማድረግ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

የልዩ ወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አብርሃም ዝናቡ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያን እያሸበረ ያለውን ወራሪ ሀይል ለመመከት በግንባር እየተዋደቀ ያለውን ጥምር ሀይል ለመደገፍ ከስንቅ ዝግጅት ባለፈ ደም የመለገስ ብሎም እስከ ግንባር በመዝመት ድጋፋችንን ለማሳየት ቆርጠን ተነስተናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ተገዳ ከገባችበት ጦርነት ተላቃ በዘላቂነት ሰላሟ እንዲረጋገጥ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የጀመረው ድጋፉ አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ማለታቸውን  የልዩ ወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡