በየካቲት ወር ከ21 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ

መጋቢት 07/2013 (ዋልታ) – በየካቲት ወር ከ21 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ዘንድሮ የተገኘው ገቢ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ12 በመቶ በላይ ዕድገት ማሳየቱ ተጠቅሷል፡፡

ሚኒስቴሩ የገቢ አሰባሰቡ ስኬታማ እንደነበረ ቢገልጽም የማይከፍሉ ዜጎች እንዳሉም አንስቷል፡፡

ደረሰኝ አለመቁረጥ፣ የግብይት ዋጋ አሳንሶ ደረሰኝ መቁረጥ፣ በሀሰተኛ ማንነት የፈጠራ ድርጅቶችን በመመስረት ሀሰተኛ ደረሰኝ አሳትሞ መጠቀምና መሸጥ፣ ወጭውን መጨመር እንዲሁም ሆነ ብሎ ገቢን መቀነስና ግብርን ለማሸሽና ለመሰወር የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸውም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሚኒስቴሩ ግብራቸውን በወቅቱ በማስታወቅ ለከፈሉ ግብር ከፋዮች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡