በየካ ክፍለ ከተማ መሬት ውስጥ ተቆፍሮ የተቀበረ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃና ሽጉጥ ተያዘ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) በየካ ክፍለ ከተማ መሬት ውስጥ ተቆፍሮ የተቀበረ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ እና ሽጉጥ በህዝብ ጥቆማ ተያዘ፡፡

ፖሊስ በመኖሪያ ቤት ባደረገው ብርበራ አንድ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ ከ28 መሰል ጥይት ጋር እንዲሁም አንድ ሽጉጥ ከመሰል 28 ጥይት ጋር መሬት ውስጥ ተቆፍረው ከተደበቁበት ሊያገኛቸው ችሏል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ቲም ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር  ካሳሁን ተሾመ በህዝብ ጥቆማ የሚደረጉ ብርበራዎች ውጤት እየተገኘባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም ለከተማችን ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን ለማስወገድ እና የተላላኪ ባንዳዎችን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ የህብረተሰቡ ጥቆማ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታቸውን አአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡