በዩኔስኮ የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ኮሚሽን የመጨረሻ ሪፖርት

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ጳጉሜ 5/2013 (ዋልታ) በፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሚመራው እና በዓለም የትምህርት የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ጥናት እንዲያደርግ በዩኔስኮ የተቋቋመው ዓለም አቅፍ ኮሚሽን የመጨረሻ ሪፖርቱን አጽድቋል።

በፈረንጆቹ የፊታችን ጥቅምት ወር ለመንግሥታቱ ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጠቅላላ ጉባዔ የሚቀርበው ይህ የጥናት ውጤት ‘’የወደፊት ዕጣዎቻችንን በጋራ ማገናዘብ’’ በሚል  ርዕስ ተጠናቅሯል፡፡

የትምህርት የወደፊት አቅጣጫ ምን መሆን አለበት በሚለው ዙሪያም ሁሉን አካታች፣ ፍትሃዊና ዘላቂ የወደፊት ዕጣዎችን ለማሳካት ትምህርት መሠረታዊ ሚና መጫወት እንዳለበት አጽንኦት ይሰጣል ተብሏል፡፡

ኮሚሽኑ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ታዋቂ የትምህርት ባለሙያዎችን ማካተቱም ተገልጿል፡፡

ሪፖርቱ በዩኔስኮ ታሪክ ሶስተኛው ሲሆን፣ በሴት እና ከታዳጊ ሀገር በመጣች ሴት ሲመራ ይህ የመጀመርያው መሆኑን ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡