በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ ለተፈናቀሉ ወገኖች 10 ሺሕ ዩሮ ድጋፍ ተሰበሰበ

ሚያዝያ 11/2014 (ዋልታ) በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ “እኔም ለሀገሬ” በሚል የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን የመረዳጃ ማኅበር በአፋር እና አማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማካሄድ 10 ሺሕ ዩሮ ድጋፍ አሰባስበዋል።

የተሰበሰበውን ድጋፍ የኢድ-አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ወደ ሀገር ቤት በመሄድ ለተረጅዎች ለማድረስ ዝግጅት መደረጉንም ፈረንሳይ ከሚገኘው ኢትዮጵያ ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸውና ለወገኖቻቸው እያሳዩት ላለው አጋርነት ኢምባሲው ምስጋና አቅርቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW