በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የበቃ ንቅናቄ ተካሄደ

ኅዳር 23/2014 (ዋልታ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የ#NO MORE (የበቃ!) ንቅናቄ በቦንጋ ከተማ ተካሄደ፡፡
አሜሪካና አንዳንድ ምዕራባዊያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያሉትን ዲፕሎማሲያዊ ጫና እና ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን በሃሰት ተፈብርከው እየቀረቡ ያሉትን ዜናዎች በመቃወም ነው የበቃ ንቅናቄ ዘመቻው የተደረገው።