በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሊያደርጉ ነው

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

ኅዳር 7/2014 (ዋልታ) በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በደቡብ ሱዳን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ተወያይቷል።

ተወያዮቹ የሕወሓትን አፍራሽ ተግባር እና ከአንዳንድ የዓለም አቀፍ አካላት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ እየደረሰ ያለውን አላስፈላጊ ጫና አውግዘዋል።

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ሕወሓት በኢትዮጵያ በተነሳ ተቃውሞ ከስልጣን መወገዱን ተከትሎ እየፈፀመ ያለውን የማተራመስ ተግባር አንስተዋል።

በተጨማሪም በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን 13 ሺሕ ዶላር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለማድረግ የገቡትን ቃል አድንቀው በኢትዮጵያ ያሉ መልካም ተግባራትን እንደሚቀጥሉ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ለአገር ክብር ሲሉ ህይወታቸውን ለሰጡ የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ እንዲሁም ለአፋር ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ የአንድ ደቂቃ የኅሊና ጸሎት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡