በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በርስቱ ይርዳው የተመራ ልዑክ በስልጤ ዞን የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኘ ነው

መጋቢት 24/ 2014 (ዋልታ) በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው የተመራ ልዑክ በስልጤ ዞን የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኘ ነው፡፡

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በስልጤ ዞን እየተገነቡ ያሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የመንንገድ እና የመስኖ ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ በነገው ዕለት በጉራጌ ዞን እየተካሄዱ ያሉ ተመሳሳይ የልማት ፕርጀክቶች ግንባታ እንደሚጎበኙም ተገልጿል፡፡