በደቡብ ክልል የማኅበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድኅን ንቅናቄ እየተካሄደ ነው

ጥር 16/2014 (ዋልታ) የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ከኢትዮጵያ ጤና መድኅን አገልግሎት ጋር በመተባበር የማኅበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድኅን ንቅናቄን እያካሄደ ነው።
አገልግሎቱ በደቡብ ክልል በ156 ወረዳዎች ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ቢያደርግም በቀጣይ ከዚህ የተሻለ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የአመራሩ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ተብሏል።
በመድረኩ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ዘርፉ ለህክምና ከኪስ የሚወጣውን ወጪ ከመቆጠብ አንፃር ፋይዳው የጎላ ነው ማለታቸውን የደሬቴድ መረጃ አመልክቷል።