ሰኔ 14/2013 (ዋልታ) – ከደሴ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኩታበር ወረዳ ነዋሪዎች ማለዳ 12:00 ጀምረው ድምፅ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በወረዳ ከተማዋ ከ72 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን፣ 6 የፖለቲካ ፓርቲዋች ይወዳደራሉ ነው የተባለው።
በኩታበር-ለ እና በበሽሎ-ለ የምርጫ ጣቢያ ተገኝተን ያነጋገርናቸው የአካባቢ ነዋሪዎች ምርጫው ያለ ምንም ተፅእኖ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።
(በቁምነገር አህመድ)