በዳንጉር ወረዳ ተጨማሪ 960 የጉሙዝ ማኅበረሰብ ክፍሎች ወደ ማዕከል ገቡ

የጉሙዝ ማኅበረሰብ ክፍሎች

የካቲት 14/2014 (ዋልታ) በበኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በጥፋት ቡድኑ በሚደርስባቸው ጫና ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ጫካ ውስጥ የነበሩ 960 የጉሙዝ ማኅበረሰቦች ወደ ወረዳ ማዕከል መግባታቸው ተገለጸ፡፡

የወረዳውን ሠላም ለማስከበር ተሰማርቶ ሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት ቅንጅታዊ ሥራ ዛሬ 960 ተጨማሪ ንፁሓን የጉምዝ ማኅበረሰብ ክፍሎች ወደ ድልሳንቢ ቀበሌ ማዕከል ገብተዋል፡፡

በወረዳው አጠቃላይ ከ5 ሺሕ 600 በላይ ነፁሓን ዜጎች በማንቡክና ድልሳንቢ ማዕከል ላይ ተጠልለው እንደሚገኙ ከክልሉ ኮሙዩኒኬሸን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።