በድብቅ የሚሰሩ ኃይሎች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ሕልውና ላይ ጥቃት ከፍተዋል – አምባሳደር ስለሺ በቀለ

መስከረም 3/2015 (ዋልታ) በድብቅ የሚሰሩ ኃይሎች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ሕልውና ላይ የከፈቱት ጥቃት መክፈታቸውን በአሜሪካ የኢትየጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ስለሺ በቀለ ገለጹ።
አምባሳደሩ አሸባሪው ሕወሓት የኢትዮጵያን ልማት ከማይፈልጉ የረጅም ጊዜ ጠላቶቿ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እያገኘ ነው ብለዋል።
በአሸባሪው ሕወሓት አማካኝነት የተጀመረው ጦርነት አንድ ቡድን ብቻ የጋረጠው ፈተና ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም ያሉት አምባሳደሩ በድብቅ የሚሰሩ አካላት በኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ሕልውና ላይ የከፈቱት ጥቃት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ሲሉ አምባሳደር ስለሺ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን የተቃጣባቸውን ጥቃት በጋራ መከላከል እንደሚገባቸው በማስመር መልእክታቸውን አምባሳደር አጠቃለዋል።