ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) በጀርመን ኑረምበርግ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ማህበር አስተባባሪነት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ለተጎዱ ወገኖች ማቋቋሚያ በተካሄደ የገቢ ማሰባሰቢያ ከአንድ ሚሊየን ዩሮ በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።
የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በተገኙበት በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ አባላቱ በቀን አንድ ዩሮ ለወገን በማዋጣት ያለማቋረጥ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
የዳያስፖራ አማካሪ ካውንስል ለማቋቋም አስተባባሪ ኮሚቴ መመረጡም ተገልጿል።
ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን በማረጋገጥ፣ ለሀገር ጥሪ ሲደረግና በራሳቸው ተነሣሽነት የመንግሥትን ሀገር የማዳን ጥሪ በመደገፍ፣ ለኢትዮጵያ አለኝታነታቸውን ማሳየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።