በጄኔቫ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ

መጋቢት 07 /2013 ዋልታ) – በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት ያለውን ትክክለኛ ሁኔታ ለማሳወቅና ጣልቃ ገብነትን በመቃወም የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።

ሰልፈኞቹ የአንድ አገር ሉዓላዊነት ሊከበር እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተለይም የህውሃት ደጋፊዎች በሚያሰራጩት ሃሰተኛ መረጃ የተነሳ በኢትዮጵያ ላይ ተገቢ ያልሆኑ ጫናዎች እየተፈጸሙ ነው ያሉት የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ትክክለኛ መረጃ በመያዝ የሚያካሂዱትን ጫና ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል።

ሰልፈኞቹ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ በህውሓት ደጋፊዎች ሃሰተኛ መረጃ የተሳሳተ ግንዘቤ መውሰድ እንደሌለባቸውም ማመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።