በጅግጅጋ ከተማ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ትምህርት ተጀመረ

መስከረም 28/2014 (ዋልታ) በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የ2014 ትምህርት ዘመን በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራ መጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የትምህርት ጥራትን የሚያሳድጉ ተግባራት በማከናወንና በቂ ዝግጀት በማድረግ ትምህርት ቤቶች መከፈታቸው የገለጸው ቢሮው፣ ከመስከረም 24 ጀምሮ በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቤቶች መደበኛ ትምህርት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የቢሮው ኃላፊ አቶ አብዱላሂ መዓሊን ተናግረዋል፡፡

ብቃት ያላቸው መምህራንን ቁጥር ለመጨመርና በአንድ ከፍል ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችን ቁጥር ከ50 ወደ 40 ዝቅ ለማድረግ መታቀዱን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡