በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ከአሜሪካ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ተወያየ

ሚያዝያ 17/2014 (ዋልታ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ ከአሜሪካ የተለያዩ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያየ።

ልዑኩ ከአሜሪካ የግምጃ ቤት፣ ውጭ ጉዳይ፣ አሜሪካ ተራድኦ ድርጅት፣ አፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ወቅት በሀገራቱ ታሪካዊ፣ ስትራቴጂክ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

ውይይቱ በዋናነት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር ተብሏል።

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!