በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ዋሺንግተን ዲሲ ገባ

ሚያዝያ 10/2014 (ዋልታ) በኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በአመታዊ የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ዋሺንግተን ዲሲ ገብቷል፡፡

ልዑኩ ዋሺንግተን እንደደረሰም ለዚሁ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ምክክር የሚጠቅመውን የመጨረሻ ዝግጅት ማድረጉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡