በጉራጌ ዞን የውትድርና ስልጠና የወሰዱ የሚሊሻ አባላት መመረቅ

የሚሊሻ አባላት መመረቅ

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) በጉራጌ ዞን መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ምልምል የሚሊሻ አባላት በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡

በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ሀገራችን ከጥንት ጀምሮ ነጻነቷን በማስጠበቅ ራሷን አስከብራ የቆየችና ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር መሆኗን አውስተዋል።

ክህደት በፈጸሙ ባንዳዎች የተቃጣብንን የጠላት ሴራ ለማክሸፍ መላው የሀገራችን ህዝብ ዳር እስከዳር በመነሳት አንድነቱን ማሳየቱንም አቶ አለማየሁ አብራርተዋል።

ባለፉት 27 ዓመታት የጥላቻና የመገፋፋት ፖለቲካ በፈጠረው ችግር ጥቂቶችን ብቻ ተጠቃሚ ያደረገ እንደነበር የተናገሩት ኃላፊው፣ ይሁን እንጂ በመላው ህዝባችን ትግል ሀገራዊ ለውጥ እውን ሆኗል ነው ያሉት።

ይህ ለውጥ ያላስደሰተው አሸባሪው ህወሓት በህዝባችን ደም ለመነገድ የጥፋት አጀንዳ ቀርጾ ሀገር እያተራመሰ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት እና ሸኔ በሀገራችን የሽብር ተግባር እየፈጸሙ መሆኑን ገልጸው፣ ተመራቂ የሚሊሻ አባላት አካባቢያቸውን ብሎም ሀገራቸውን ለመጠበቅ ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሀገራችን ነጻነቷን አስጠብቃ መቀጠል እንድትችል መላው የሀገራችን እና የክልሉ ህዝቦች በህልውና ዘመቻው ላይ እያደረጉት ያለውን ትግል እንዲያጠናክሩ አቶ አለማየሁ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችን ይከተሉ

አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!