በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዙሪያ በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ሙሉቀን ሀፍቱ (ዶ/ር)ና 11 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው

 

መስከረም 11/2015 (ዋልታ) በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዙሪያ ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ አልተወጡም በሚል የመንግሥትን ስራ በማይመች አኳኋን በመምራት በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ሙሉቀን ሀፍቱ (ዶ/ር) እና 11 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው።

የአዲስ አበባ የቴክኒክ ሙያ ስልጠናና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሙሉቀን ሀፍቱን (ዶ/ር) ጨምሮ 11 ግለሰቦች የመንግሥትን ስራ በማይመች አኳኋን በመምራት ከባድ የሙስና ወንጀል ነው የተከሰሱት።

ከተከሳሾቹ መካከል ሙሉቀን (ዶ/ር) ይመሩት ከነበረው መስሪያ ቤት አብርሃም ሴርሜሎ፣ ኩምሳ ቶላ እና መብራቱ ኪዳነማሪያም እንዲሁም ከቤቶች አስተዳደር ባዩልኝ ረታ፣ ሚኪያስ ቶሌራ እና ዮናስ ወ/ጊዮርጊስ ይገኙበታል።

በግለሰቦቹ ላይ የተመሰረቱት ክሶችም የመንግሥትን ስራ በማይመች አኳኋን መምራትና በስልጣን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል እንዲሁም በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ናቸው ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW