በግጭት ለተጎዱ ከ5 ሺሕ በላይ ቤተሰቦች ድጋፍ ተደረገ

ግንቦት 22/2014 (ዋልታ) የዓለም ዐቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በቄለም ወለጋ፣ ሃዋ ገላንና ስዮ ወረዳ ለሚገኙ በግጭት ለተጎዱ 5 ሺሕ 143 ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ድጋፉ የስንዴ፣ ባቄላ እና ማሽላ ዘርን ያካተተ መሆኑንም ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የማዳበሪያና የግብርና ግብአቶችን ለመግዛት የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ይደረጋል ብሏል።