በጎንደርና አካባቢዋ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ምክክር እየተካሔደ ነው

የካቲት 26/2014 (ዋልታ) በጎንደርና አካባቢዋ የሚስተዋሉ የፀጥታ እና የዕድገት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ምክክር እየተካሔደ ነው።

የጎንደር ሰላምና ዕድገት ማኅበር (ጎ.ሰ.ማ) ከጎንደር ልማት ማኅበር (ጎ.ል.ማ) በጋራ በመሆን በአሁኑ ወቅት የጎንደርን ታሪክ በማይመጥን መልኩ ሥርዓት አልበኝነት እየተንሰራፋ በመምጣቱ ይህንን ችግር ለመፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር እየተካሔደ ነው ተብሏል።

የጎንደር ሰላም ለአማራ ሰላም የአማራ ሰላም መሆን የኢትዮጵያ ሰላም መሆኑን ያነሱት የጎንደር ሰላምና ዕድገት ማኅበር ሰብሳቢ ደሳለኝ በላቸው በጎንደርና አካባቢዎች የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት መመካከርና ከመንግሥት ጎን በመሆን የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዙፋን አምባቸው