በጎንደር ከተማ ለህልውና ዘመቻው የመጀመሪያ ዙር ወጣቶች ተመረቁ

ሐምሌ 29/2013 (ዋልታ) – በጎንደር ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ዙር የዘመቻ ለህልውና ዘማች ወጣት ምሩቃን የምረቃ ስነ ስርአት ተካሄደ።

የጎንደር ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ ሞላ መልካሙ ለህልውና ስጋት  የሆነውንየትህነግ ቡድን እየጠፋ መሆኑን ገልጸው በዚህ ታሪካዊ ወቅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ታሪክ መስራቱ ትልቅ እድል ነውና የዚህ ታሪክ ተሳታፊ እንሁን ብለዋል፡፡

የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻችን እንዲሁም የአማራ ወጣቶች አሸባሪው ትህነግን ወደ መቃብር ለመሸኘት በዝግጅት ላይ ይገኛል ማለታቸውን ከጎንደር ከተማ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።