በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገባ

ግንቦት 25/2014 (ዋልታ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉብኝት ባሌ ሮቤ ገብቷል።
በጉብኝቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተጨማሪ የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኡስማን ዲዮን እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ናቸው።
የልዑካን ቡድኑ በባሌ ዞን እየተከናወኑ ያሉ የግብርና ሥራዎችን ተዘዋውሮ ይመለከታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢብኮ ዘግቧል፡፡