በጣሊያንና ግሪክ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ውይይት ተደረገ

ታኅሣሥ 4/2014 (ዋልታ) በጣሊያንና ግሪክ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች እና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚደረገውን ድጋፍ አስተባብሮ በሚላክበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የበይነ መረብ ውይይቱ የተካሄደው፡፡

በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ የሽብርተኛው ሕወሓት ቡድን በአገሪቱ የሚስተዋለው ችግርና እየደረሰ ያለውን ያልተገባ የውጭ ጫናን ለመመከት ዳያስፖራው  እያደረገው ያለውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አድንቀዋል።

የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ አመራሮች ስለገንዘብ አሰባሰብ እና መላኪያ መንገዶች ገለፃ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ኃላፊዎችም ስለአይዞን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አጠቃቀም በተመለከተም ገለፃ አድርገዋል።