በጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው የነበሩ የደርግ ባለስልጣናት የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተሻሻለ

ላለፉት 30 አመታት አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው በነበሩት የደርግ ባለስልጣናት ላይ ተላልፎ የነበረው የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተሻሻለ፡፡

ማሻሻያውንም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በፊርማቸው አጽድቀዋል። ማሻሻያው የጸደቀላቸው ለሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህና ሌተናል ጄኔራል አዲስ ተድላ ናቸው።

ከፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በቀድሞዎቹ ባለስልጣናት ላይ ተላልፎ የነበረው የሞት ፍርድ ወደ እድሜ ልክ እስራት ተሻሽሎላቸዋል፡፡