በፓሪስ ኦሊምፒክ የወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

አትሌት ታምራት ቶላ

ነሐሴ 4/2016 (አዲስ ዋልታ) በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ በወንዶች ማራቶን ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ።

አትሌት ታምራት ከ30 ኪሎ ሜትር ጀምሮ ውድድሩን ሲመራ ቆይቶ በሸአናፊነት ያጠናቀቀ ሲሆን 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ 26 ሰኮንድ በመግባት ነው ሩጫውን ያጠናቀቀው።

ኢትዮጵያ በፓሪሱ ኦሊምፒክ ያገኘችው የመጀመሪያው ወርቅ ሆኖም ተመዝግቧል።

በውድድሩ ኢትዮጵያን ወክለው የተወዳደሩት አትሌት ደሬሳ ገለታ በአራተኛነት ሲያጠናቅቅ ቀነኒሳ በቀለ 39ኛ በመሆኑን ውድድሩን ማጠናቀቅ ችለዋል።

እንኳን ደስ አለን!