በ138 ሚሊዮን ብር የተገነባው የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ቢሮ ተመረቀ

ነሐሴ 19/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በ138 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባውን የወልዲያ ከተማ የአስተዳደር ህንጻ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

የህንፃው ግንባታ በ2009 ዓ.ም ተጀምሮ በበጀት ችግር ሲጓተት እንደቆየና በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት መብቃቱን የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዳዊት መለሰ (ዶ/ር) በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

138 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትን የከተማ አስተዳደሩ ህንጻ የክልሉ መንግሥት በግብዓት ማሟላት ሂደት እገዛ እዲያደርግም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው መጠየቃቸውን ከሰሜን ወሎ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ከተማዋ ወደ ሪጂዮፖሊታን ከተማነት ደረጃ ማደጓን ተከትሎ የምስጋና መርኃ ግብር በወልዲያ ከተማ ሺህ አል አላሙድ ዘመናዊ ስታድዮም እየተካሄደ ይገኛል።

በመርኃ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፈንቱ ተስፋዬን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ከወልዲያ ከተማ ሕዝብ ጋር ታድመዋል።

የወልዲያ ከተማ ለ5 ወራት በአሸባሪው ሕወሓት ቁጥጥር ሥር ሆና በርካታ ግፍ ማስተናገዷንም መረጃው አስታውሷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW