በ2030 የጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ጥቅምት 1/2015 (ዋልታ) በ2030 የጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

ለዚህም 24.2 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት የደረጃ 3 የጨቅላ ህፃናት ጽኑ ህክምና ማእከል መገንባቱን
የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገልፀዋል።

በጤና ሴክተሮች ላይ የመንግስት ቁርጠኝነት የማህበረሰብ ተሣትፎና የአጋር ድርጅቶች ርብርብ የሚጠበቀውን ግብ ለማምጣት እንደሚረዳ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የዮኒሴፍ ዳይሬክተር ዶ/ር መሰረት ዘላለም በበኩላቸው በዓመት የሚሞቱትን የ116 ሺሕ ህፃናት ሞትን ለመቀነስ የጤና ባለሙያዎችን ማብቃት ጨምሮ ለእናቶችና ህፃናት አስፈላጊውን ክብካቤ ለመስጠት ከUNICEF ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የዮኒሴፍ ተወካይ ዶ/ር ጃን ሙያቲ የኢትዮጵያ መንግስት የህፃናት ሞትን ለመቀነስ እየሰራ ያለውን ጥረት አድንቀው በትብብር በመስራት የጨቅላ ህፃናቱን ሞት መታደግ ይጠበቃል ብለዋል።

ብሩክታዊት አፈሩ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW