በ36ኛው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጉባኤ የተሳተፉ የአገራት መሪዎች ወደ አገራቸው ተሸኙ

የካቲት 13/2015 (ዋልታ) በአዲስ አበባ የተካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጉባዔ መጠናቀቅን ተከትሎ የተለያዩ አገራት መሪዎች ወደ አገራቸው መሸኘታቸው ተገለጸ፡፡

በዚህም የኬንያ፣ ሴኔጋል፣ ሩዋንዳ፣ ሞሮኮ፣ ማዳጋስካር፣ አልጄሪያ፣ ኮንጎ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻድ፣ ጋና፣ ቦትስዋና፣ ናይጄሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሲሸልስ እና ብሩንዲ መሪዎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በተጨማሪም የሌሴቶ፣ አንጎላ፣ ጋቦን፣ ጅቡቲ፣ ኒጀር፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ፍልስጤም እና የሴራሊዮን መሪዎች ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ለመሪዎቹ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናትም ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡

ቀሪዎቹ መሪዎችም ዛሬ ማምሻውን ወደ አገራቸው ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ መረጃዎች አመላክቷል፡፡