በ8 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የተገነባው የጊንጪ ሃይል ማከፋፈያ ዛሬ ይመረቃል

መጋቢት 11/2013 (ዋልታ) – በ8 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተገነባው የጊንጪ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ዛሬ ይመረቃል።
የምረቃ ስነ-ስርዓቱ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በሚገኙበት ይከናወናል።
ኤ.ዲ.ዲ.ኤም እና ጂ የተሰኘው ፕሮጀክት አካል የሆነው የጊንጪ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ 230/15 ኪሎ ቮልት ሲሆን ሁለት ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች ተገጥመውለታል።
የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያው እስከ 100 ሜጋ ዋት የመሸከም አቅም ሲኖረው አስር ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮችም አሉት።
ላርሰን ኤንድ ቱርቦ የተሰኘ የሕንድ ኩባንያ ግንባታውን ያከናወነው ሲሆን፤ ኤም.ቪ.ቪ ዲከን የተባሉ የጀርመንና ስዊዘርላንድ ኩባንያ የማማከር ሥራውን ሰርተዋል።
ላርሰን ኤንድ ቱርቦ የሚገነባቸው አራት የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች አቃቂ ቁጥር 2፣ ደብረዘይት ቁጥር 3፣ ዱከም ቁጥር ሁለትና ጊንጪ ቁጥር 2 አጠቃላይ ግንባታቸው 56 ሚሊየን ዶላር ነው።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የጊንጪ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለከተማዋና ለአካባቢው አስተማማኝ ሃይል ማቅረብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።