በ9ኛው የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ፖሊስ አትሌቶች አሸነፉ

ጥቅምት 27/2015 (ዋልታ) 9ኛው የ30 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ፖሊስ አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል።

ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ በተካሄደው የጎዳና ሩጫ ውድድር በወንዶች የኢትዮጵያ ንግዱ ባንኩ ፋንታሁን ሁነኛው አንደኛ ሆኖ አጠናቋል።

ሌላኛው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌት መኳንንት አየነው ሁለተኛ ሲወጣ የግል ተወዳዳሪው አብዱ አስፋው 3ተኛ ሆኖ ጨርሷል።

በሴቶች በተደረገ ውድድር ደግሞ የኦሮሚያ ፖሊሷ አጸደ ባይሳ አንደኛ ስትወጣ የመቻል አትሌቲክስ ክለብን የወከለችው ፍቅርተ ወለታ ሁለተኛ የንግድ ባንኳ ብዙሃገር አደራ 3ተኛ ሆነው ጨርሰዋል።

የኦሮሚያ ፖሊስ በአጠቃላይ ውጤት በሴቶች አሸንፎ ዋንጫውን ሲወስድ በወንዶች ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቡድን ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።

በዘንድሮ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የአንጋፋ አትሌቶች ውድድር በሁለቱም ጾታ ሲደረግ ከ50 አመት በላይ እና በታች በተደረጉ ውድድሮች ከአንድ እስከ 6 ለወጡ አትሌቶች የሜዳሊያ እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷል።

በ30 ኪ.ሜ ውድድር በሁለቱም ጾታ ከ1 እስከ 8 የወጡ አትሌቶች የሜዳሊያ እና የገንዘብ ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዶች ተረክበዋል።

በትዝታ ወንድሙ